የመስቀል ጦርነቶች

ዓለም ከአስተናገደቻቸው አስከፊና አሰቃቂ የፓለቲካ፣ የዳር ድንበር እንዲሁም የዘር ጦርነቶች ባልተናነሰ የአይማኖት ጦርነቶችንም አስተናግዳለች።
ስስና አይነኬ በመባል በሚጠራው የአይማኖት ጉዳይ አማካኝነት ወንድም ከወንድሙ፣እህትም ከእህቶ ሳይቀር ጎራ በመክፈል እርስበርሳቸው ደም ተፋሰዋል።
በዚህች  የሰው ልጆች እንደመኖሪያ ቤታችን በምንጠቀምባት ዓለም ውስጥ ብዙ አስከፊና መራራ የአይማኖት ጦርነቶች የተካሄዱባት ሲሆን ከነሱም ውስጥ የመስቀል ጦርነት  
(Crusade) በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።
ከእየሱስ ክርስቶስ ልደት በሆላ ከ1095 እስከ 1204 ባሉት 109 አመታት ውስጥ 4 የመስቀል ጦርነቶች የተደረጉ ሲሆን በነዚህም ጦርነቶች አማካኝነት ከ5 ሚሊየን ያላነሰ 
ህዝብ ህይወቱን አጥቶል።
እነዚህ የመስቀል ጦርነቶች አብዛኞቹ በዘመኑ በነበሩ የአይማኖት አባቶች ወይም ጳጳሳት አማካኝነት የተመሩ ሲሆን ለጳጳሳቱ ወደn ጦርነት መግባት  እንደምክንያት ሆኖ የሚ
ጠቀሰውበታላቁ መፅሐፍ ወይም በመፅሐፍ-ቅዱስ ውስጥ ቅድስቲቶ ምድር (holly land) ተብላ የተጠቀሰችውን እየሩሳሌምንና በዙሪያዋ የሚገኙትን ከተሞችን ከወራሪዎች 
እጅ ለመንጠቅ በሚል ነው።
በነዚህ ተከታታይ 4 የመስቀል ጦርነትቶች  ውስጥ የመስቀል ጦረኞች በማን ተመሩ? አላማቸውስ ምነበር? እንዴትስ ተጠናቀቀ? የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ከዚህ በታች
ባጭሩ እንያቸው።
         አንደኛው የመስቀል ጦርነት 
በPope Urban 2ኛ፣ Walter The Penniless እንዲሁም በPeter The Hermite በጋራ በተካሄደው የመጀመርያው የመስቀል ጦርነት 1095 እስከ 1099 ለ4
አመታት የፈጀ ሲሆን አላማቸውም አንቲያክንና እየሩሳሌምን ይዞ የመስቀል ጦር ግዛቶች ማድረግ ነበር ይህም አላማቸው ሰርቶ ጦርነቱን በአሸናፊነት አጠናቅቀዋል።
images-1.jpg
  ሁለተኛው የመስቀል ጦርነት
በPope Eugenus 3ኛ፣ በEmperor Konrad 3ኛ፣በLouis 5ኛ እንዲሁም በBerard of clarivaux ትብብር የተደረገው ሁለተኛው የመስቀል
ጦርነት ከ1147 አስከ 1149  የፈጀ ሲሆን አላማውም በሙስሊም ጦረኞች ግዛት ስር የነበረችውን የኤዳሰን ከተማን ለመያዝ ነበር። ነገር ግን በጦርነቱ በመሸነፋ
ቸው አላማቸው ሳይሰምር ቀርቶል አልፎ ተርፎ ቀድሞ በቁጥጥራቸው ስር የነበሩትን ከተሞችንም አጥተዋል
images-3.jpg

    ሶስተኛ የመስቀል ጦርነት
ይሄ ሶስተኛው የመስቀል ጦርነት በወቅቱ ስማቸው ገኖ በነበረው የጦር ሜዳ ጀግኖች በነ Richard The lion-Hearted፣ በEmperor Fredic Barbar
ossa፣ በphilip Augutus እና King of Frace ቅንጅት ከ1189 እስከ 1192 የተደረገ ጦርነት ሲሆን። በSaladin እጅስር የገባችውን እየሩሳሌም ዳግም
ለማስመለስ  የታቀደ ጦርነት ነበር ነገር ግን በሽንፈት ምክንያት ሳይሳካላቸው ቀርቶል!
images-2.jpg
አራተኛው የመስቀል ጦርነት
በ1198 በpope innocent II አማካኝነት የተጠረውና በፈረንሳይ የመስቀል ጦረኞች የተሳተፋበት ከ1202 እስከ 1204 የፈጀው 4ኛው የመስቀል ጦርነት
ክርስትያኖችን የኋይልና የሞራል ውድቀት ላይ ጥሎ ነው ያለፈው። የሙስሊሞችን ኋይል ከእስራሄልና ከአጎራባች አገሮች ማስወጣት ዓላማው አርጎ የተነሳው
ይህ አራተኛው የመስቀል ጦርነት እንዳሰቡት ሳይሳካ ከመጠናቀቁ በላይ በቁጥጥራቸው ስር የነበሩትን የኮንስታንቲኖፕል(Constantinople) እና የዛራ(Zara) ግዛቶች
አጥተውበታል።
images-4.jpg

Comments