የመስቀል ጦርነቶች ዓለም ከአስተናገደቻቸው አስከፊና አሰቃቂ የፓለቲካ፣ የዳር ድንበር እንዲሁም የዘር ጦርነቶች ባልተናነሰ የአይማኖት ጦርነቶችንም አስተናግዳለች። ስስና አይነኬ በመባል በሚጠራው የአይማኖት ጉዳይ አማካኝነት ወንድም ከወንድሙ፣እህትም ከእህቶ ሳይቀር ጎራ በመክፈል እርስበርሳቸው ደም ተፋሰዋል። በዚህች የሰው ልጆች እንደመኖሪያ ቤታችን በምንጠቀምባት ዓለም ውስጥ ብዙ አስከፊና መራራ የአይማኖት ጦርነቶች የተካሄዱባት ሲሆን ከነሱም ውስጥ የመስቀል ጦርነት (Crusade) በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። ከእየሱስ ክርስቶስ ልደት በሆላ ከ1095 እስከ 1204 ባሉት 109 አመታት ውስጥ 4 የመስቀል ጦርነቶች የተደረጉ ሲሆን በነዚህም ጦርነቶች አማካኝነት ከ5 ሚሊየን ያላነሰ ህዝብ ህይወቱን አጥቶል። እነዚህ የመስቀል ጦርነቶች አብዛኞቹ በዘመኑ በነበሩ የአይማኖት አባቶች ወይም ጳጳሳት አማካኝነት የተመሩ ሲሆን ለጳጳሳቱ ወደn ጦርነት መግባት እንደምክንያት ሆኖ የሚ ጠቀሰውበታላቁ መፅሐፍ ወይም በመፅሐፍ-ቅዱስ ውስጥ ቅድስቲቶ ምድር (holly land) ተብላ የተጠቀሰችውን እየሩሳሌምንና በዙሪያዋ የሚገኙትን ከተሞችን ከወራሪዎች እጅ ለመንጠቅ በሚል ነው። በነዚህ ተከታታይ 4 የመስቀል ጦርነትቶች ውስጥ የመስቀል ጦረኞች በማን ተመሩ? አላማቸውስ ምነበር? እንዴትስ ተጠናቀቀ? የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ከዚህ በታች ባጭሩ እንያቸው። አንደኛው የመስቀል ጦርነት በPope Urban 2ኛ፣ Wa...